የልዩ ድጎማ ማመልከቻ መመሪያዎች

Instruk­tioner till ansökan om särskilt bidrag – amhariska

1. የግል መረጃ

ማመልከቻው ለሚመለከተው ሰው የግል መረጃን ይሙሉ።

2. የፋይናንስ ሁኔታዎን ሪፖርት ያድርጉ

  • 2.1. እርስዎ እና አጋርዎ ከስራ ወይም ከሌላ ባለስልጣን ወይም ድርጅት የሚያገኙት ደሞዝ፡ ድጎማ፡ ለምሳሌ ብሕመም ጊዜ የሚከፈሉ ጥቅሞች፣ የወላጅ ድጎማ ወይም ከማሕበራዊ ኢንሹራንስ የሚገኝ ጥቅማጥቅሞችን ካሉ፡ ሙሉ። ማመልከቻው ለአንድ ልጅ የቀረበ ከሆነ፡ የወላጆች ገቢም መሞላት አለበት። ገቢው በኣሃዝ ይጻፉ።
  • 2.2. እርስዎ እና አጋርዎ ከስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ ሊያገኙ ከሚችሉት የቀን አበል የበለጠ፡ የካሽ ገንዘብ ካሎት ይሙሉ። ማመልከቻው የተደረገው ለአንድ ልጅ ከሆነ፡ የወላጆቹ የካሽ ገንዘብ እንዲሁ መሞላት አለበት። ገንዘቡ በኣሃዝ ይጻፉ።
  • 2.3. እርስዎ እና አጋርዎ የገንዘብ ሀብቶች ካሉዎት፣ ለምሳሌ መኪና፣ በስዊድን ውስጥ ወይም በውጭ አገር የባንክ ፈንዶች፣ የእራስዎ ኩባንያ፣ አክሲዮኖች ወይም በውጭ አገር ገንዘብ ለማግኘት መሸጥ የሚችሉትን ንብረት፡ ካለ ይሙሉ። ማመልከቻው ለአንድ ልጅ የቀረበ ከሆነ፡ የወላጆቹ ንብረቶችም መሞላት አለባቸው። የገንዘብ ሃብቶቹ ብኣሃዝ ይጻፉ።

3. ፌርማ

ማመልከቻውን በመፈረም፡ በእውቅና እና በሙሉ ፈቃደኝነት የሚያረጋግጡት

  • በማመልከቻው ውስጥ ያቀረቡት መረጃ ትክክል መሆኑ
  • የገንዘብ ድጎማን የማግኘት መብትዎን ወይም መጠኑን ሊነኩ የሚችሉ ለውጦችን ሪፖርት የማድረግ ግዴታ እንዳለብዎት
  • በስህተት የቀረቡ መረጃዎች እንደ ገበን ሊታዩ እንደሚችሉና፡ ወደ ፖሊስ ክስም ሊያቀርብ እንደሚችል እንደሚያቁ
  • እየፈረሙት ያለ፡ የተረዳዎት እንደሆነ

4. የልዩ ድጎማ የጥቅል ምርጫ

ለልዩ ድጎማ የሚያመለክቱበትን ጥቅል ላይ ምልክት ያድርጉ። ለልዩ ድጎማ ለማመልከት የሚፈልጉት ከጥቅሎቹ ጋር የማይጣጣም ከሆነ፡ ወደ ነጥብ 5 (ሕክምና እና መድኃኒት) ወይም ነጥብ 6 ይቀጥሉ።

5. ለጤና እንክብካቤ እና ለመድኃኒት ወጪዎች የልዩ ድጎማ ማመልከቻ

ለማመልከት ለሚፈልጉት ሳጥኑ ላይ ምልክት ያድርጉ እና ከዚያ ድጎማው ለምን እንደሚያስፈልግ በተቻለ መጠን በዝርዝር ይግለጹ። ስም ያለበት፡ ማንኛውንም ደረሰኞች እና የሐኪም ማዘዣ ዝርዝሮችን፡ ያያይዙ።

6. ከመደበኛ ጥቅሎች ጋር የማይጣጣም ከሆነ ፍላጎትዎን ይግለጹ

ለልዩ ድጎማ ለማመልከት የሚፈልጉት ነገር በቁጥር 4 ወይም 5 ላይ የማይመጥን ከሆነ፡ ድጎማው ለምን እንደሚያስፈልግ እና እቃውን ወይም አገልግሎቱን ለመግዛት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ በሚገባ ይግለፁ። ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለምን እንደሚያስፈልግዎም ይግለፁ። ከማመልከቻው ጋር የሚልክዋቸው የትኞቹን ሰነዶች እንደሚያስገቡ ይፃፉ።

የስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ ተጨማሪ መረጃ ሳይጠይቁ ውሳኔ እንዲሰጡ ማመልከቻውን በትክክል መሙላት አስፈላጊ ነው። ምንም አይነት መረጃ ከሌለ የስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ የእርስዎን ፍላጎት መገምገም ስለማይቻል ማመልከቻዎን ውድቅ ለማድረግ ሊወስን ይችላል።

የማመልከቻው ቅጹን ወደ መቀበያ ክፍል ያስገቡ ወይም ወደ መቀበያ ክፍል ይላኩ።

የስዊዲን የስደተኞች ኤጀንሲ መቀበያ ክፍሎች፡ የፖስታ አድራሻዎች Opens in new window.

Last updated: