ለጤና ክብካቤ የሚወጣ ወጪ
Avgifter för sjukvård – amhariska
የ LMA ካርዳቸውን ለሚያሳዩ የጥገኝነት ፈላጊዎች እነኚህ ክፍያዎች ተገቢ ናቸው፡፡
የጉብኝቱ ዓይነት | ክፍያ |
---|---|
በጤና ክብካቤ ማዕከላት ውስጥ የዶክተሮች ቀጠሮ | 50 ክሮነር |
ከሪፈራል* በኋላ የዶክተሮች ቀጠሮ | 50 ክሮነር |
ከሪፈራል* በኋላ ከዶክተሩ ይልቅ ወደ ሌላ የጤና ክብካቤ ሰጪ (ለምሳሌ ነርስ፣ ፊዚዮቴራፒስት፣ አማካሪ) | 25 ክሮነር |
የህጻናት እና ቅድመ ወሊድ ህክምና፣ የእርግዝና ክብካቤ እና የህጻናት ወሊድ | ነጻ |
ተላላፊ በሽታ ካለብህ የመከላል ህክምና | ነጻ |
*ሪፈራል ማለት አንድ ህመምተኛ ልዩ የሆነ ምርመራ ወይም ህክምና ሲያስፈልገው ዶክተሩ ወደ ሌላ የጤና ክብካቤ ሰጪ ክሊኒክ የሚልከው የመግባቢያ ወረቀት ነው፡፡ የሪፈራል ወረቀቱ ስለሚታይብህ የህመም ምልክቶች፣ ስለ ስሜትህ እና የበፊት የህምም ታሪክህ እና ቁስል ካለህ በዝርዝር የሚይዝ ነው፡፡ የጤና ክብካቤ ሰጪው ክሊኒክ - የሪፈራል ወረቀቱን የሚቀበልህ - ለምርመራ ይጠራሃል፡፡
ከባድ የሆስፒታል ክብካቤ
ለከባድ ታማሚዎች የሚጠየቀው ክፍያ ከሀገር ሀገር ይለያያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ያለውን የክፍያ መጠን ከሀገሪቱ ምክር ቤት/ከክልሉ ድህረ ገጽ ላይ ወይም በ 1177 ቫርደጉይደን ማግኘት ትችላለህ፡፡
የጉብኝቱ ዓይነት | ክፍያ |
---|---|
ወደ ብሔራዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎት ወይንም ወደ ሌላ የጥርስ ህክምና ሰጪ የጥርስ ሃኪም የሚደረግ አጣዳፊ ህክምና | 50 ክሮነር |
ከብሔራዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎት እውቅና ውጪ ወደ ግል የጥርስ ሃኪም ለድንገተኛ ህክምና መሄድ | ሃኪሙ የሚያስከፍለንን |
ለጤና ማዕከል ሂሳብ የሚከፍሉበት መንገድ
የጤና ማዕከላትን፥ ማለትም ሆስፒታል፡ ጤና ጣቢያ ወይም የጥርስ ህክምና ዘንድ ሲሄዱ፥ በዚያው የአገልግሎት ሂሳብዎን እንዴት መክፈል እንደሚችሉ፥ ሁሌ መጠየቅ ይኖርብዎታል። ከጤና ማዕከሉን ግልጋሎት በማግኘትዎ ምክንያት ሂሳብ እንደየሚኖሩበት ከተማ በተለያየ መንገድ ይከፍላሉ። አንዳንድ ጤና ማዕከሎች በጉብኝትዎ ወቅት ሂሳብዎን እዚያው በካርድ ወይም በካሽ ይቀበላሉ። ሌሎቹ ሂሳብዎን ቤትዎ ድረስ ይልካሉ። የጤና አገልግሎት ሰጭው በፋክቱር ብቻ ሂሳብ የሚያስከፍል ከሆነ፥ ወደ ቦታው ተመልሰው በመምጣት መክፈል የሚችሉ መሆንዎን ይጠይቁ። ምክንያቱም፡ ጥገኝነት ጠያቂዎች፡ በፋክቱር ለመክፈል ያላቸው ዕድል በጣም አነስተኛ በመሆኑ ነው።
መድሃኒቶች
ሃኪም ለሚያዝልህ መድሃኒቶች በአብዛኛው የምትከፍለው 50 ክሮነር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚታዘዙልህ መድሃኒቶች ከ 50 ክሮነር በላይ ውድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ለህፃናት የሚታዘዙ መድሃኒቶች ነጻ ናቸው፡፡
ለህመምተኛ የሚሆን ትራንስፖርት
ለህመምተኛው ትራንስፖርት ከ40 ክሮነር ያልበለጠ ትከፍላለህ፡፡
ከስደተኞች ቦርድ የሚደረግ ድጋፍ
ለጤና ክብካቤ ያወጣሃቸውን ወጪዎች እንዲሁም ለመድሃኒት ግዢ ያወጣሃቸውን ወጪዎች ከታዘዘበት ወረቀት ጋር ይዘህ ልዩ ድጋፍ እንዲደረግልህ የስደተኞች ቦርድን መጠየቅ ትችላለህ፡፡
ወጪዎችህ ከ 400 ክሮነር ከበለጡ
በ 6 ወራት ውስጥ ለዶክተሮች ቀጠሮ፣ ለህመምተኛ ትራንስፖርት፣ ለታዘዙ መድሃኒቶች እና ለሌላ የጤና ክብካቤዎች (እንደ ፊዚዮቴራፒ ላሉ) ያወጣኸው ወጪ ከ 400 ክሮነር ከበለጠ ልዩ ድጋፍ እንዲደረግልህ ማመልከት ትችላለህ፡፡ የስደተኞች ቦርድ ከ 400 ክሮነር ለሚበልጡ ወጪዎች ሽፋን ይሰጥሃል፡፡ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲደረግልህ ለአገልግሎቱ የከፈልክበትን ደረሰኝ (የክፍያ መጠን ሳይሆን) ለማረጋገጫ ማሳየት አለብህ፡፡ የመድሃኒቶቸን ደረሰኝ በተመለከተ በታዘዘልህ መሰረት ማቅረብ ይኖርብሃል - በደረሰኙ ላይ ስምህ ሊጠቀስ ይገባል፡፡
ከአንድ የጤና ማዕከል፥ የሃኪም መሸኛ ደብዳቤ (remiss) ሳይኖርዎት በግልዎ አንድ ስፔሻሊስት ሃኪም ጋር ከተገናኙ ከፍ ያለ ተመን ይጠየቃሉ። ክፍያው ከፍተኛ-ወጪ-መጠበቂያ (högkostnadsskyddet) ውስጥ አይታሰብም። ማለትም የከፈሉት 400 ክሮኖር አይታሰብም ማለት ነው።
ከባድ የጤና ክብካቤ እና መድሃኒት
ለከባድ የጤና ክብካቤ የሚወጡ ወጪዎች ከላይ በተጠቀሰው የ400 ክሮነር ውስጥ የሚጠቃለሉ አይደለም - ነገር ግን ከ50 ክሮነር ለሚበልጥ ወጪ ልዩ ድጋፍ እዲደረግልህ መጠየቅ ትችላለህ፡፡ ከባድ የጥርስ ህመም አጋጥሞህ የብሔራዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎት ክፍት ያልነበረ ከሆነ ወይንም አንተ አጣዳፊ አገልግሎት ፈልገህ ጊዜ ያልነበራቸው ከሆነ በተመሳሳይ መልኩ የምትስተናገድ ይሆናል፡፡ ደረሰኙን ወደ ስደተኞች ቦርድ ይዘህ ሄደህ የልዩ ድጋፍ ማመልከቻህን ህክምናውን ከታከምክ በኋላ በፍጥነት አስገባ፡፡
ጥያቄዎ ውድቅ ከሆነ
ይግባኝ ሊጠይቁበት የማይቻል ወደ መጡበት እንዲመለሱ ወይም ከአገር እንዲወጡ የሚል ውሳኔ በሰጠቱ ምክንያት ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ያልዎት የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብትዎ ከታገደ (LMA kort) መታዎቂያዎን ይመልሳሉ፥ ለመድሃኒት መግዣም ሆነ ሃኪም መጎብኛ ገንዘብም ማግኘት አይችሉም።