ለሚኖሩበት ቤት መክፈል የሚገባዎት የገንዘብ መጠን
Så mycket ska du betala för boendet – amhariska
እናንት የጥገኝነት ማመልከቻ ያስገባችሁ ወይም ደግሞ በገፍ ለመጡ ስደተኞች በወጣው መመሪያ መሰረት ግዚያዊ ከለላ የተሰጣችሁ፣ ብሎም በስደተኞች ጉ/ ጽህፈት ቤት ወይም በኮሙዩን በኩል መኖሪያ ቤት ያገኛችሁ፣ በደሞዝ መልክ ገቢ ወይም ሌላ የገንዘብ ማግኛ ምንጭ ያላችሁ ከሆነ፥ ለምትኖሩበት ቤት የተወሰነ ክፍያ መፈጸም ይኖርባችኋል። ለመኖሪያ ቤቱ የምትከፍሉት የገንዘብ መጠን የሚወሰነው በቤተሰብ አባላት ብዛት ከመሆኑ በተጨማሪ በመኖሪያ ስፍራችሁ ውስጥ የምግብ አገልግሎት የሚሰጣችሁ መሆኑም ከግምት ይገባል።
በጋብቻ ተሳስረው አንድ ላይ የሚኖሩና ሳይጋቡ አንድ ላይ የሚኖሩ ሰዎች የቤተሰቡን ኢኮኖሚ በተመለከተ የጋራ ሃላፊነት አላችው። ከአብሮ ኗሪዎቹ አንዱ ብቻ የራሱ ገቢ ያለው ከሆነ ወይም (ሴትዋንም ይመለከታል) ያ ሰው ለራሱና ለኑሮ ጓደኛው እንዲሁም ለልጆቹ የመኖሪያ ቤት ወጪ መክፈል ይኖርበታል። የኢኮኖሚዎ መጠን በሚለወጥበት ግዜ ለመስተንግዶ ክፍላችን ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።
የምግብ አገልግሎት በማይሰጥበት መኖሪያ ሰፈር፣ አንድ አዋቂ ለሚኖርበት ቤት በወር 2100 ክሮኖር ይከፍላል፣ ለልጁ ደግሞ 1050 ክሮኖር ይከፍላል። የልጆች ብዛት ከሁለት በላይ ቢሆንም ቤተስቡ እንዲከፍል የሚጠየቀው ለሁለት ልጆች ብቻ ነው።
ምሳሌ
የምግብ አገልግሎት በማይሰጥበት የመኖሪያ ሰፈር የሚቀመጡ ሁለት በአንድ ቤት ከሶስት ልጆቻቸው ጋር አብረው የሚኖሩ ወላጆች (አዋቂዎች)፣ አንዱ ወላጅ ብቻ ወይም ሁለቱም ወላጆች ሥራ ቢኖራቸውም/ ባይኖራቸውም ቤተሰቡ ለሁለቱ ወላጆችና ለሁለቱ ልጆች የመኖሪያ ወጪ መሸፈን ይኖርበታል፣
2 100 ክሮኖር + 2 100 ክሮኖር + 1 050 ክሮኖር + 1 050 ክሮኖር = 6 300 ክሮኖር
ቤተሰቡ ለሶስተኛው ልጅ መክፈል አይኖርበትም።
የምግብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የመኖሪያ ቤቶች
በአንዳንድ መኖሪያ ሰፈሮች የጋራ መዓድ ቤት ውስጥ የምግብ አገልግሎት ይሰጣል። የምግብ አገልግሎት በሚሰጥባቸው መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የምትኖሩ ሰዎች፣ ለሚቀርብላችሁ ምግብ፣ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ትከፍሉበታላችሁ፣ አንዳንዴ የሚቀርበውን ምግብ መብላት ባትፈልጉም እንኳ መክፈል ይኖርባችሃል።
በመኖሪያ ሰፈራችሁ ምግብ የሚቀርብላችሁ ከሆነ፣ በየወሩ ለመኖሪያ ቤቱ ከምትከፍሉት ገንዘብ በተጨማሪ ለምግብ አገልግሎትም ትከፍላላችሁ፣
- 1 410 kr በወር - ለአንድ ብቸኛ አዋቂ ሰው
- 1 260 ክሮኖር በወር፣ አብረው ለሚኖሩ ወይም ተጋብተው አንድ ላይ በአንድ ቤት ለሚኖሩ፣
- 1 260 ክሮኖር በወር፣ እየተማሩ ከወላጆቻቸው ጋር ለሚኖሩ 18-20 ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ወጣቶች
- 750 kr በወር- እስከ 3 ዓመት ዕድሜ ልጅ
- 930 kr በወር- ከ4 እስከ 10 ዓመት ልጅ
- 1 140 kr በወር- ከ 11 እስከ 17 ዓመት ልጅ
ለምግብ አገልግሎት፣ ቤተሰቡ ውስጥ ለሚኖሩ ለሁሉም ልጆች ይከፈልላቸዋል።
ልዩ ምክንያት
ከሥራ የሚያገኙት ደሞዝ ወይም ሌላ የገቢ ምንጭ ቢኖርዎትም፣ ለምግብ እና ለመኖሪያ ቤት መክፈል የማይገደዱበት ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ የሚሆነው ከሥራ የሚያገኙት ደሞዝ ወይም ከሌላው የገቢ ምንጭ የሚያገኙት የገንዘብ መጠን፣ የምግብ እና የመኖሪያ ቤትዎን ወጪ ከሸፈነ በኋላ የሚቀርዎት ገንዘብ ከተገቢው ሀገራዊ ራስ ማስተዳደሪያ ገንዘብ መጥን (riksnormen för försörjningsstöd) በታች ከሆነ ነው። ይህ የራስ ማስተዳደሪያ የገንዘብ መጠን በማሕበራዊ ኑሮ ጉዳይ ዋና ጽ/ ቤት (socialstyrelse) የሚወሰን ሲሆን፥ በየዓመቱ ማስተካከያ ይደረግበታል። ኢኮኖሚዎ ምን እንደሚመስል ለጽሕፈት ቤታችን መስተንግዶ ክፍል ይንገሩ፣ ለመኖሪያ ቤትዎ እና ለምግብ ወጪ ራስዎ መክፈል እንዳለብዎትና እንደሌለቦት የሚገነዘቡበትን ሂሳብ ለማስላት ድጋፍ ያገኛሉ።