የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ያመልክቱ
Ansök om provisoriskt främlingspass – amhariska
አንድ መደበኛ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት የማይችሉ ከሆነ ወይም ፓስፖርቱን ለማውጣት የሚፈጀውን ግዜ መጠበቅ የማይችሉበት ሁኔታ ከገጠሞት አንድ ግዜያዊ የጉዞ ሰነድ ወይም ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ይችላሉ። ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት የሚጸናው ለአጭር ግዜ ወይም ለአንድ የተወሰነ ጉዞ ብቻ ነው።
ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት እንዲጠይቁ የተገደዱበት ምክንያት | ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማግኘት ማሟላት የሚገባዎት ጉዳይ |
---|---|
የአገርዎን ፓስፖርት ሆነ ሌላ ተቀባይነት ያለው የጉዞ ሰነድ፣ ወደ ሌላ አገር ሄደው ካላመለከቱ በቀር፣ እዚሁ ስዊድን ውስጥ እንዳሉ ማግኘት የሚችሉበት ምንም መንገድ የለም። | ከስዊድን ውጭ ተጉዘው የአገርዎን ፓስፖርት መቼ፣ የት ሄደውና በምን መንገድ ማውጣት የሚችሉበትን የጉዞ ዕቅድ አለዎት። |
እጅግ አስቸኳይ በሆነ ጉዳይ ወደ ውጭ አገር በፍጥነት ለመሄድ ቢያስፈልግዎትና እና፥ የአገርዎ ፓስፖርት ባይኖርዎት። | በአሁኑ ሰዓት የእንግዳ ፓስፖርት ለምን እንዳስፈለግዎ እና በምን ምክንያት የአገርዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ከአገርዎ ባለስልጣናት፣ ለምሳሌ ከአገርዎ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ማግኘት እንዳልቻሉ ለስዊድን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት መግለጽ ይኖርብዎታል። ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ሲያመለክቱ፣ ችግርዎን የሚያስረዱ ሰነዶች ካለዎት ይዘው ይምጡ። |
ቀድሞ የነበርዎት የልዩ ጥገኛ የጉዞ ሰነድ (resedokument) ወይም የእንግዳ ፓስፖርት የሚጸናበት ግዜ በማለፉ ምክንያት ወይም በከባድ የወንጀል ክስ የተፈረደቦት በመሆንዎ ምክንያት የእንግዳ ፓስፖርት ሊያገኙ አልቻሉም። ይሁን እንጂ ወደ ውጭ ለመጓዝ የሚያበቃዎ እጅግ አጣዳፊ ምክንያት ስላለዎት መጓዝ የግድ ሆኖብዎታል። | በአሁኑ ሰዓት የእንግዳ ፓስፖርት ለምን እንዳስፈለግዎ እና በምን ምክንያት የአገርዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ከአገርዎ ባለስልጣናት፣ ለምሳሌ ከአገርዎ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ማግኘት እንዳልቻሉ ለስዊድን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት መግለጽ ይኖርብዎታል። ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ሲያመለክቱ፣ ችግርዎን የሚያስረዱ ሰነዶች ካለዎት ይዘው ይምጡ። |
የስዊድን አገር የመኖሪያ ፈቃድ እያለዎት (ከመጡበት አገር ሳይህን ማለት ነው) ውጭ አገር ወጥተው ባሉበት ሰዓት የእንድግዳ ፓስፖርትዎ ወይም የጉዞ ሰነድዎ በመጥፋቱ ምክንያት ወደ ስዊድን ለመመለስ ፓስፖርት ለማግኘት ኣስፈላጊነቱ ቢያጋጥምዎት። | ፓስፖርትዎ መጥፋቱን በወቅቱ ለሚገኙበት አገር ፖሊስ ያመለክታሉ፣ ክዚያም ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለመጠይቅ በዚያ አገር ከሚገኘው የስዊድን ኤምበሲ ወይም የስዊድን ቆንስላ ዘንዳ፥ የፖሊስ ማመልከቻውን ግልባጭ ወይም ኮፒ ይዘው ይሄዳሉ። |
ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት በዚህ መንገድ ያመለክታሉ
ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት፥ (ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማመልከት) ”Ansökan om provisoriskt främlingspass, 192011” የሚል ቅጽ ሞልተው ካበቁ በኋላ፥ በአካል ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሄደው ማመልከቻውን ያስገባሉ።
ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች
ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በራሳቸው ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው መጠየቅ የለባቸውም። በእነሱ ፈንታ መጥየቅ የሚችለው የልጁ አሳዳጊ ወይም ሞግዚት መሆኑ በህግ የሚታወቀው ሰው ራሱ በግሉ ነው።
የልጁ አሳዳጊዎች ተብለው በህግ የሚታወቁት ሰዎች ሁለት ከሆኑ፥ (የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች (የእንግዳ ፓስፖርት ወይ የጉዞ ሰነድ) እንዲሰጥ ፈቃድ መስጫ ሰነድ)፥ “Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass (främlingspass eller resedokument) för barn under 18 år, 246011”፥ የሚለው ቅጽ ላይ የሰፈርውን ውል ሁለቱም አሳዳጊዎች መቀበላቸውን በፊርማቸው ማረጋገጥና፥ ይህንኑ በሁለት እማኞች ማስመስከር ይኖርባቸዋል።
እንደ ልጁ ሞግዚት ሆነው ማመልከቻ የሚያስገቡ ከሆነ ሞግዚትነትዎ የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰንድና የመታወቂያ ወረቀትዎን ኮፒ ከማመልከቻው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርብዎታል።
ወላጆቹ ስዊድን ውስጥ የማይቀመጡ ልጅ ፎቶግራፍ ለመነሳትና የጣት አሻራውን ለመስጠት ሲመጣ፥ ሞግዚቱ ከልጁ ጋር አብሮት በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት መገኘት ይኖርበታል።
ቀነ ቀጠሮ
ማመልከቻ ለማስገባት ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከመምጣትዎ በፊት ቀነ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት የሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው ለየራሱ ቀጠሮ መያዝ እና ለያንዳንዱ ሰው የየራሱን ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልጋል። ብዙ ቀነ ቀጥሮች በቅደም ተከተል መያዝ ይቻላል።
በውጭ አገር የሚገኙ ከሆነና ወደ ስዊድን ለመመለስ ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት የሚፈልጉበት ሁኔታ ከተፈጠረ፥ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኘው የስዊድን ኤምበሲ ወይም የቆንስላ ጽ/ ቤት ዘንድ ሄደው ምን ማድረግ እንዳለብዎት መረጃ ይጠይቁ።
ማመልከቻ ያስገቡ
ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ግዜ የሚከተሉትን መያዝ አይዘንጉ
- የማመልከቻ ቅጽ፣ የተሞላ እና የተፈረመበት (አንድ ቅጽ ለአንድ ሰው)
- ቀደም ብሎ ያወጡት የእንግዳ ፓስፖርት ካለዎት
- የአገርዎ ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነትዎን የሚገልጽ ሰነድ ወይም መታወቂያ (የሆነ ፓስፖርት ከሌለዎት ማለት ነው) ለምሳሌ ያህል የተለመደው መታወቂያ ካርድ፣ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም የውትድርና ደብተር ሊያቀርቡ ይችላሉ።
- ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ ማመልከቻውን እንዲያስገባ ከወላጆቹ ወይም ከሕጋዊ ሞግዚቱ የይሁንታ ፈቃድ መስጫ፥ ማለትም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ልጁ የእንግዳ ፓስፖርት እንዲሰጥው መፍቀዱን የሚገልጽ ቅጽ (Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass (främlingspass eller resedokument) för barn under 18 år (የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች (የእንግዳ ፓስፖርት ወይ የጉዞ ሰነድ) እንዲሰጥ ፈቃድ መስጫ ሰነድ), 246011) ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በፊት የነበርዎት የእንግዳ ፓስፖርት በመጥፋቱ ምክንያት፥ አዲስ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ካለብዎት፣ የእንግዳ ፓስፖርቱ መጥፋቱን የሚጠቅስ መረጃ የያዘ ከፖሊስ የተሰጥዎትን ሰነድ ግልባጭ ወይም ኮፒ
- ከስዊድን ውጭ ተጉዘው የአገርዎን ፓስፖርት ማውጣት አስበው ከሆንና ይህን ጉዳይ ለመፈጸም ወደ ትውልድ ሃገርዎ መጓዝ ካለብዎት ወይም የሃገርዎ ኤምበሲ ወደ ሚገኝበት አገር መጓዝ ካለብዎት፣ መቼ፣ የትና እንዴት አድርገው ማውጣት እንደፈለጉ የሚገልጽና የጉዞ ዕቅዶን የሚያሳይ የጉዞ ካርታ፣
የትውልድ ሃገርዎ ፓስፖርት ወይም አሮጌ የእንግዳ ፓስፖርት ካለዎት ለስድተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤት (Migrationsverket) ማስረከብ ይኖርብዎታል። አንዳንድ ግዜ ጉዳዩን የያዘችው የስድተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤት ጸሃፊ ከኦርጅናሉ ይልቅ የፓስፖርትዎን ኮፒ ከማመልከቻዎ ጋር እንዲሰጡ ልትጠይቅዎት ትችላለህ። ይሁን እንጂ ማመልከቻዎ መታየት ሲጀምር ወይም ውሳኔ ተሰጥቶበት አዲሱን ፓስፖርት ሊያወጡ ሲመጡ ኦሪጂናሉን ፓስፖርት እንዲያስረክቡ መጠየቅዎ አይቀርም።
ማመልከቻ ሊያስገቡ በሚመጡበት ግዜ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ፎቶግራፍ ያነሳዎታል፣ የጣት አሻራዎንም ይወስዳል። የተነሱት ፎቶግራፍ፣ የጣት አሻራዎ እና ሌሎች የግልዎ መረጃዎች በሙሉ የግዚያው እንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ በተለጠፈችው ኤሌክትሮኒክ ካርድ ውስጥ ይቀመጣሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ዘንድ የሚቀመጥ እርስዎን የሚመለከት ምንም መረጃ አይኖርም፣ እነዚህ መረጃዎች የሚቀመጡት እዚያው ፓስፖርቱ ላይ በተለጠፈችው ትንሽ ኤለክትሮኒክ ካርድ ወይም ቺፕ ውስጥ ብቻ ነው። ከ6 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የጣት አሻራ እንዲሰጡ አይጠበቅባቸውም።