የስደተኛ ፈቃድ ለተሰጣቸው ሰዎች የመኖሪያ ፈቃድ ስለመስጠት
Uppehållstillstånd för dig som har fått status som flykting – amhariska
የስደተኛ ፈቃድ ከተሰጣችሁ ለሦስት ዓመት የመኖሪያ ፈቃድም ይሰጣችኋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ራሳችሁን ማስተዳደር ከቻላችሁ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡
ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃዳችሁ በስዊድን ሀገር ውስጥ ለሦስት ዓመታት ለመኖር እና ለመሥራት የሚያስችል መብት ይሰጣችኋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ እንደ ማንኛውም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንደተሰጠው ሰው ሕክምና የማግኘት ተመሳሳይ መብት አላችሁ፡፡
የመኖሪያ ፈቃድ እንዳላችሁ የሚያሳይ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይሰጣችኋል፡፡ ይህ ካር መታወቂያ ወረቅት ወይም የጉዞ ዶክመንት አይደለም፡፡ የመኖሪያ ፈቃድህ የጸና እስከሆነ ድረስ ከአገር መውጣትና መግባት ትችላለህ፣ ይሁን እንጂ ከስዊድን ወጥተህ ተመልሰህ ለመግባት አንድ የጸና ፓስፖርትና የጸና የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ መያዝ ይኖርብሃል።
በሕዝብ ምዝገባ ዶሴ ላይ መመዝገብ
ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ በስዊድን ግብር ኤጄንስ ውስጥ በሚገኘው የሕዝብ መመዝገቢያ ዶሴ (ስካተቨርከት) ላይ በተቻለ ፍጥነት መመዝገብ አለብዎ፡፡ ስዊድንኛ ለስደተኞች (ኤስ ሴፍ አይ) የሚለውን ትምህርት ከመማራችሁ በፊት መመዝገብ ይርባችኋል እንዲሁም ስትመዘገቡ የስዊድን ማህበራዊ ጥበቃ ሲስተም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ መሆን አለብዎ፡፡ በስዊድን ሕዝብ መዝገብ ውስጥ ስትመዘገብ ለአንዳንድ ነገሮች፣ ለምሳሌ የባንክ ደብተር እና የኤለክትሮኒክ መታወቂያ (e-legitimation) የመሳሰሉትን ለማውጣት፣ የሚጠቅምህ የስዊድን አገር የመታወቂያ ሰነድ ማግኘት ትችላለህ።
በስዊድን የሕዝብ መመዝገቢያ ዶሴ ላይ ለመመዝገብ ወደ ስዊድን ግብር ኤጀንሲ በመሄድ መመዝገብ ይኖርባችኋል፣ ኤጀንሲውም አድራሻዎትን፣ የትዳር ሁኔታችሁ (ያገቡ ወይም ያላገቡ እንደሆነ)፣ ዜግነታችሁን እና የትውልድ ቦታ ይመዘገባል፡፡ ወደ ግብር ኤጀንስ ሲሄዱ የመኖሪያ ፈቃድ ካርዶን እና ሕጋዊ የሆነ መታወቂያ ማምጣት ይኖርባችኋል፡፡ መታወቂያዎ በስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ የተያዘ እንደሆነ ቅጂ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ቅጂው ከዋናው ጋር አንድ እደሆነ ቅጂውን በሚሰጠው ሰው መፈረም አለበት፡፡ የሚያረጋግጠውም ሰው ስሙን በትክክለኛው ፊደል (ካፒታል ሌተር) መጻፍ እና ስልክ ቁጥሩን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
በሕዝብ ምዝገባ ላይ የስዊድን ታክስ ኤጄንስ መረጃ (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.
የመቋቋሚያ ድጋፍ እርምጃዎች
በቅርቡ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያገኛችሁ፥ እዚህ ሥራ ለመስራት መብት ኣላችሁ፤ ወደ ሥራው ዓለም ለመግባት ደረጃ የሚያስችል መቋቋሚያ ድጋፍ የማግኘት መብትም አላችሁ። የመቋቋሚያ ድጋፍ፥ ከሚሰጠው ዕርዳታ ውስጥ የስዊድንኛ ቋንቋ መማርን፥ ወደ ሥራው ዓለም ወደ መግባት ደረጃ የሚያደርሱና ራስን መቻልን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ይገኙበታል። የመቋቋሚያ ድጋፍን የመስጠትና ሥራ የማፈላለጉ ኃላፊነት ያለው ባለ ስልጣን፤ የስዊድን የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ተቋም (Arbetsförmedlingen) ነው።
“የስራ ማፈላለጊያ ቢሮ” (Arbetsförmedlingen)፥ ዕድሜዎ 65 ዓመት እስኪሞላ ድረስ፣ ስራ በማፈላለግ ሊረዳዎት ይችላል። ይህ ዕድሜ፡ በስዊድን የተለመደ የጡረታ ዕድሜ ነው። ዕድሜያቸው ከገፋ በኋላ ወደ ስዊድን የሚመጡ ሰዎች የሚያገኙት የጡረታ ደሞዝ አብዛኛውን ግዜ አነስተኛ ወይም ምንም ይሆናል። እርስዎ፣ ለመተዳደሪያዎ የሚበቃ የጡረታ ደሞዝ የማያገኙ ከሆነ ወደ “ጡረታ ጉዳይ ባለስልጣን” (Pensionsmyndigheten) በማቅናት፥ “በዕድሜ የገፉ ሰዎች የመተዳደሪያ ድጋፍ” የሚጠይቁበት (äldreförsörjningsstöd) የተሰኘውን” ማመልክቻ ሞልተው ያስገባሉ።
ስለ “በዕድሜ የገፉ ሰዎች መተዳደሪያ ድጋፍ”፡ በጡረታ ጉዳይ ባለስልጣን፡ በስዊድንኛ የበለጠ ያንብቡ። External link, opens in new window.
በስዊድን ሀገር ውስጥ ሥራ ስለ መሥራት
በሶስት ዓመት የጊዜ ገደብ የተወሰነ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጣችሁ፥ ስዊድን ውስጥ ተቀጥራችሁ መስራት ትችላላችሁ። የመኖሪያ ፈቃዳችሁ የጊዜ ገደብ በሚያበቃበት ወቅት ራሳችሁን ማስተዳደር የምትችሉበት ሥራ ካላችሁ፥ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የመጠየቅ ዕድል አላችሁ።
ለስራ በሚያመለክቱበት ወቅት በስዊድን ሀገር ውስጥ ለመኖር እና ለመሥራት ፈቃድ እንደተሰጣችሁ የሚያሳዩ መረጃዎቻችሁን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመኖሪያ ፈቃድ ካርዳችሁን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ቀጣሪዎቻችሁ በስዊድን ሀገር ውስጥ ለምን ያኽል ጊዜ መስራት እንደተፈቀደላቸሁ ማወቅ ይፈልጋሉ እንዲሁም በስዊድን ውስት ለመስራት የተሰጥዎ ፈቃድ ምን ክከላ እንዳለበት ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡
የቤተሰብ ቅልቅል
እንደ አንድ ጥገኛ መኖሪያ ፈቃድ የተሰጥዎት እንደሆነ፥ እንዲሁም ረዘም ላለ ግዜ የሚቆይ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሰጥዎት የሚያስችል ጥሩ የተስፋ ምክንያት አለ ተብሎ ከተገመገመ፥ ቤተሰቦችዎ ወደ እርሶ ወደ ስዊድን አገር ለመምጣት ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ።
የቅርብ ቤተ-ሰቦችዎ ብቻ ናቸው ወደ ስዊድን ወደ እርሶ ለመምጣት የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባት የሚችሉ። ቤተ ሰቦችዎ የሚሰጣችው የፈቃድ ግዜ ርዝመት፥ የእርሶ ፈቃድ ጸንቶ እስከሚቆይበት ዕለት ድረስ ነው።
የስድራቤት መልሶ መገናኘት መብት ካሎት፥ ራስን የማስተዳደር ግዴታም የሚመልከትዎት ሊሆን ይችላል። ይህ ማለት፡ እርሶዎና ቤተሰብዎ በሚገባ ለመኖር የሚያስፈልግ ወጪ፥ እርስዎ ራስዎ መሸፈን ይኖርብዎታል። በተጨማሪም ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን ሲመጡ፥ ከእርሶ ጋር የሚኖሩበት፡ በመጠንና በጥራት ደረጃው የጠበቀ መኖሪያ ቤት ሊያዘጋጁ የገቧታል። ራስን ከማስተዳደር ግዴታ ሌላ አስተያየት የሚደረግለት ሁኔታ ኣለ፥ ለምሳሌ እርስዎ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙበት ቀን ጀምሮ፥ ቤተሰብዎ ሶስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ካስገቡ፥ ራስን የማስተዳደር ግዴታ ደንብ እርስዎ አይመለከቶትም።
ከቤተሰብ ጋር ስለመገናኘት እና ለዚህ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ተጨማሪ አንብብ፡፡
የመኖሪያ ፈቃድ ሊነጠቅ ይችላል
ለመኖሪያ ፈቃድ ሲያመለክቱ የውሸት ማስረጃ ከሰጡ፣ አውቀው ከዋሹ ወይም ለመኖሪያ ፈቃድ አስፈላጊ የሆነ ማስረጃን ሆን ብለው ከደበቁ የመኖርያ ፈቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡ ወንጀል ሠርተው ተፈርዶቦት ከሆነ ፍርድ ቤት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ሊወስን ይችላል፡፡ ከዚያም የስደተኞች ኤጀንሲው የመኖሪያ ፈቃድዎን ይሰርዘዋል፡፡ ምንም እንኳ ለብዙ ዓመታት የመኖርያ ፈቃዱ የተሰጦት ቢሆንም የመኖሪያ ፈቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ስለማራዘም
በግዜ የተገደበ የመኖሪያ ፈቃድዎ ሲያልቅ፥ ፈቃዱን ለማራዛም ማመልከቻ የማስገባት መብት ኣሎት። ያኔም ከለላ የሚያስፈልግዎት ሆነ ከተገኘ፥ የመኖሪያ ፈቃድዎ ሊራዘምልዎት ይችላል። ከሶስት ዓመት በኋላም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ።
የመኖሪያ ፈቃድ ይዛችሁ ወደ ስዊድን የመጣችሁ አዲስ እንግዶች የሚያስፈልጋችሁ መረጃ
የመኖሪያ ፈቃድ ውሳኔ የተሰጠበትን ሰነድ በደንብ ያስቀምጡት። የመንግሥት ባለሥልጣናትና አንዳንድ ተቋማት ጋር ሲገናኙ ያሰነድ ይጠቀሙበታል።
እንደ ነዋሪ በሃገር አስተዳደር የሕዝብ መዝገብ (folkbokföring) ውስጥ እንዲመዘገቡና የስዊድን መለያ ልዩ ቁጥር (personnummer) እንዲያገኙ የቀረጥ ጽ/ ቤትን Skatteverket External link, opens in new window.ሄደው ማነጋገር ያስፈልጋል።
በማኅበራዊ የመድን ስርዓት ውስጥ ለመመዝገብ ”ፎርሸክሪንግስካሳ” Försäkringskassan External link, opens in new window. የሚባለውን መንግሥታዊ ተቋም ይጎብኙ።
አንዳንድ ኮሙዩኖች የሚከራዩ ቤቶችን የሚያፈላልጉ መስሪያ ቤቶች (bostadsförmedling) አሏቸው። የሚከራይ ቤት ለማግኘት ከነዚህ መስሪያ ቤቶች ዘንድ ሄደው መመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪ ኮሙዩኖች በአካባቢያቸው ስላሉ የግል ቤት አከራዮች መረጃ ሊሰጥዎች ይችላሉ።
የሚኖሩበት ኮሙዩን የሕፃናት እንክብካቤ ማዕከልና የልጆች ትምህርት ቤት ስላለው ለልጅዎ ያዘጋጅልዎታል።
ጤናና ሕክምናን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት የሚኖሩበትን አውራጃ ጽ/ቤት ያነጋግሩ። በመላው አገር የጤና ጥበቃ መረጃ እዚህ ያግኙ 1177 Vårdguiden. External link, opens in new window.
ስዊድንኛ ለመጤዎች (SFI) ስለሚባለውን ትምህርት ጥያቄ ካለዎት የሚኖሩበትን ኮሙዩን ጽ/ቤት ያነጋግሩ። ለተጨማሪ መረጃ ይህን ድረገጽ ይጎብኙ። Sveriges kommuner och regioner. External link, opens in new window.
ሥራ በሚፈልጉበት ግዜ ሥራ ማፈላለጊያ ተቋም Arbetsförmedlingen External link, opens in new window. ድረስ ሄደው ይመዝገቡ።
ዕድሜያችሁ ከገፋ በኋላ ወደ ስዊድን ለመጣችሁና በመካያው የጡረታ ደሞዛችሁ አነስተኛ ወይም ምንም ለሆነባችሁ፣ ጡረታ ጉዳይ ባለስልጣን Pensionsmyndigheten External link, opens in new window. በዕድሜ የገፉ ሰዎች የመተዳደሪያ ድጋፍ (äldreförsörjningsstöd) የሚጠይቁበት፥ በስዊድንኛ ተጨማሪ ማብራሪያ አለው።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በዩኒቨርሲቲዎች ስለሚሰጡ ትምህርቶች መረጃ ለማግኘት ወደነዚህ Antagning.se External link, opens in new window. ወይም studera.nu External link, opens in new window. ድረገጻት ጎራ ይበሉ።
በትምህርት ላይ በሚቆዩበት ግዜ ስለሚሰጥ የመተዳደሪያ ገንዘብ (studiemedel) ጥያቄ ካለዎት CSN, Centrala studiestödsnämnden External link, opens in new window. ይጎብኙ።
መንጃ ፈቃድን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት የትራንስፖርት ጉዳይ ጽ/ ቤትን Transportstyrelsen External link, opens in new window. ማነጋገር ይችላሉ።
በፖለቲካ ጉዳይ የመምረጥና መመረጥ መብትዎን በተመለከተ የሚጠይቁት ጉዳይ ካለ Valmyndigheten External link, opens in new window. ከሚባለው ባለ ሥልጣን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በስዊድን ስላለው ትምህርት ነክ ጉዳይን በተመለከተ፥ ከትምህርት ቤቶች ባለሥልጣን (Skolverket) Om svenska skolan External link, opens in new window. መረጃ ይውሰዱ።
ስለ ስዊድንን ማህበራዊ ጉዳይ አጠቃላይ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች በ Information om Sverige External link, opens in new window. ማግኘት ይችላሉ።
ስለ ስዊድንን ማህበራዊ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ደግሞ ይህን Svenska institutet ይህን ደረገጽ External link, opens in new window.ይጎብኙ።
Hej hej Sverige! External link, opens in new window. ስዊድን እንዴት እንደምትንቀሳቀሰ የሚያሳይ ቀላልና ቀሰቃሽ በሆነ መንገድ የተሰራ ፊልም መመልከት የሚችሉበት ድረገጽ ነው።
Lära svenska በ www.informationsverige.se External link, opens in new window. የተባለው ድረገጽ ውስጥ ስዊድንኛ በግልዎ ሊማሩ የሚያስችሎት የተለያዩ ፕሮግራሞች ያገኛሉ።
Konsumentverkets upplysningstjänst External link, opens in new window. የግዢና ሽያጭ ውልን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት መረጃ ያገኙበታል።