የተለየ የወሲብ ዝንባሌ ሲኖሮዎትና - ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑ

För dig som är hbtq-person och söker asyl – amhariska

በወሲባዊ ዝንባሌዎ ወይም በጾታዎ ወይም ጾታዬ እንዲህ ነው በማለትዎ ወይም በጾታዊ ማንነትዎ ወይም የአንድ የተወሰነ ህብረተ ሰብ ክፍል አካል በመሆንዎ ምክንያት ማሳደድ እንደሚደርስብዎት አውቀው ጽኑ አመክንዮ ያለው ፍርሃት ውስጥ የሚገኙ ከሆነ፣ ስዊድን ውስጥ ጥገኛ የመሆንና ለደህንነትዎ ከለላ የማግኘት መብት ይኖርዎታል። ይህ ስደተኞችን እስመልክቶ በወጣው አለም አቀፍ የስምምነት ሰነድ ላይ፣ የስዊድን ህገ ደንብ ውስጥ እንዲሁም በአውሮፓ ሕብረት ህገ ደንብ ውስጥ ሰፍሮ የሚገኝ ድንጋጌ ነው።

ጥገኝነት ስለ መጠየቅና ደንቦቹ

ማሳደድ ሲባል፡ በህይወትዎ ወይም በጤናዎ ላይ አደጋ ለማድረስ የሚደረግ ዛቻ ወይም ጥቃት ሊሆን ይችላል። ይህ ብቻ ኣይደለም፣ ባለዎት ወሲባዊ ዝንባሌ ምክንያት ህጎችና ደንቦች ወይም የህብረተ ሰብ አመለካከት በእርስዎ ላይ የሚያደርሰው ክፉ የጥላቻ ዘመቻ ሊሆንም ይችላል። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ፥ በቅጣት መልክ ወይም ለይቶ በመነጠል፣ ለምሳሌ ትምህርት ቤት በመከልከል፣ ስራ ወይም ህክምና እንዳትመርጥ በማድረግ ሊተገበር ይችላል።

የሆነ ጎሳ ወይም ዘር አባል መሆንዎ ወይም የአንድ እርስዎ የመረጡት እምነት ተከታይ መሆንዎ ወይም ጾታዎ ወይም የወሲብ ዝንባሌዎ ምክንያት ጥቃት ይደርስብኛል ብለው ሳይፈሩ ሐሳብዎን በነጻ የመግለጽና በፖለቲካ ጉዳዮች የመሳተፍ መብትዎ መነካት፥ ስዊድን ውስጥ ለመቆየት ከሚያስችሉ ምክንያቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።

በእርስዎ ላይ ጥቃት ሊያደርስ የሚዝትቡዎት የሃገርዎ መንግስት ባለስልጣናት ወይም የራስዎ ቤተሰብ ወይም ሌሎች ሰዎች መሆናቸው ምንም ለውጥ አያመጣም። ቀጥሎ፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፣ (Migrationsverket) እርስዎ ወደ ፊት ወደ ሃገርዎ ቢመለሱ የሃገርዎ ባላስልጣናት እርስዎን፣ ሊደርስብኝ ይችላል ከሚሉት፣ ጥቃት ሊታድግዎት የማይችሉ ወይም የማይፈልጉ መሆናቸውን ያጣራል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት (Migrationsverket) እርስዎን እንደ አንድ ስደተኛ ጥያቄዎን ሲያስተናግድ፣ ስምዎን፣ የተወለዱበትን ዘመንና በህግ የሚታወቀውን ጾታዎን የሚመዘግበው ልክ መታወቂያዎ ላይ የሰፈረውን መሰረት በማድረግ ነው። በስዊድን ህግ መሰረት በሌላ ስም ልንመዘግብዎት አይፈቀድም፣ ይሁን እንጂ መጠሪያዎ እንዲሆንዎ የሚፈልጉት ስም ወይም ተውላጠ ስም ካለዎት ለኛ ቢነግሩን፣ ነገሩን በመዝገብ ይዘን የምናቆየው ይሆናል።

ምርመራ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት (Migrationsverket) ለደህንነትዎ ከለላ የሚያስፍልጎት መሆንዎን፣ ብሎም የስዊድን መኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጥዎ ከመወሰኑ በፊት የእርስዎ ህይወት ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ግንዘቤ ለማግኘት ይጥራል፣ እርስዎም እንድ አንድ ግለ ሰብ ለምን ወደ ትውልድ ሃገርዎ መመለስ እንደፈሩ ያጣራል። የፈሩበት ምክንያት ወሲባዊው ዝንባሌዎ ወይም ጾታዎን በራስዎ ስሜት በመግለጽዎ ወይም በጾታ ማንነትዎ ከሆነ በተቻለ መጠን ቀደም ብለው እንዲገልጹልን ያስፈልጋል።

ጥገኝነት እንዴት እንደሚያመለክቱ እዚህ በይበልጥ ያንብቡ

ይህን መሰል፥ ወሲብና ጾታ ነክ ነገሮችን ከዚህ በፊት አግኝተውት ለማያውቁት ሰው ማውራት ከባድ ሊሆን እንደሚችል የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የሚገነዘበው ጉዳይ ነው። ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱን የግል ጉዳይ ለሌላ ሰው ሲያወሩ የመጀመሪያዎ ግዜዎ ሊሆን ይችላል። የግልና የራስ ብቻ የሚባሉ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁሉም ሰው የሚያበጀው የራሱ ድንበሮች አሉት፥ ድንበሮቹ እንድየ ሰው የተለያዩ ናቸው። ያም ሆነ ይህ፣ ለጥገኝነት ጥያቄዎ ምክንያት ነው የሚሉትን መረጃ በሙሉ በተቻልዎት መጠን ለኛ መግለጹ በጣም አስፈላጊ ነው። እንደተባለው በተቻለ መጠን ዘርዝረው ሲያቀርቡ፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትም ውሳኔ ለመስጠት የተሻለ መሰረት ያገኛል ። ጉዳዩን የሚያጣራው ጸሐፊያችን፣ ስለ እርስዎ የወሲብ ዝንባሌ እና እርስዎ ራስዎን የሚገልጹበት የጾታ ወገን ወይም የጾታ ማንነትዎን አስመልክቶ የነበርዎት ሃሳብና ስሜት እንዲሁም ከቤተሰብ፣ ከጓደኞችና ከሚኖሩበት ማሕበርሰብ ጋር የነበርዎትን ግንኙነቶች የሚመለከቱ ጥያቀዎች ያቀርብሎታል። እኛ የሰውን ምስጢር የመጠበቅ ህጋዊ ግደታ ስለ አለብን፥ እርስዎ ለኛ የነገሩንን፣ ጉዳዩ ከሚመለከተው ሰራተኛ በቀር፣ ለማንም አናስተላልፍም።

የርስዎን ጉዳይ ምርመራ የየያዘው የስደተኞች ጽ/ቤት ሰራተኛ፣ እርስዎ የሚነግሩትን ጉዳይ የተገነዘበ መስሎ የማይታይዎት ከሆነ ወይም ሰራተኛው ያልጠየቅዎት ግን እርስዎ የያዙት መረጃ ካለዎት በተቻለ ፍጥነት መናገር ይኖርብዎታል። በጥገኝነት ጥያቄው ላይ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ አይጠብቁ።

በርሶ የጥገኝነት ጥያቄ ሂደት ወቅት፣ እርስዎ በተቻለ መጠን መረጋጋትና ደህንነት እንዲሰማዎት፥ አስተርጓሚው፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኛ ወይም እርስዎን ወክሎ የሚቆመው ሰው ጾታ ላይ፥ የበኩልዎን ምርጫ ማቅረብ ይችላሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትም በምርጫዎ መሰረት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል። እናንት ከ18 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆናችሁ ሰዎች፣ ከናንተ ጋር አብሮዋቹ የመጡ ሰዎች ሳይጨመሩበት፥ ህጋዊ ወኪላችሁን እና ጉዳያችሁን የሚያስተናግደውን የስደተኞች ጽ/ቤት ሰራተኛን የምታገኙት ብቻችሁን ነው። በጾታዊ መድልዎና ጥቃት ላይ ልዩ ዕውቀት ያለው ሰው ህጋዊ ውክልና እንዲይዝልዎት፣ የሚያውቁት ካለም መጠቆም ወይም እኛ እንድናፈላልግሎት ሃስብዎን ማቅረብ ይችላሉ።

ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ለሆናችሁ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ጥገኝነት የሚጠይቁ ልጆችን በሙሉ በጥሞና ያዳምጣል፥ ለደህንነታቸው ከለላ ያስፈልጋቸው እንደሆንም በሚገባ ይመረምራል። ስለዚህ በትውልድ ሃገራችሁ ውስጥ ትኖሩ በነበረበት ወቅት የነበራችሁበትን ሁኔታ ማስረዳትና ወደ እዚያው ወደ ሃገራችሁ ብትመለሱም ሊገጥማችሁ ይችላል ብላቹ የምታምኑት ችግር፥ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤቱ በሚገባ መግለጽ በጣም አስፈላጊ ነው። ዕድሜያችሁ ከ18 ዓመት በታች የሆናችሁና አሳዳጊዎቻችሁ እዚሁ ስዊድን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እነሱ ክፍሉ ውስጥ በሌሉበት ከናንተ ጋር ብቻችሁን ማነጋገር እንችል እንደሆነ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በቅድሚያ ወላጆቻችሁን ፈቃድ ይጠይቃል። ወላጆቻችሁ እዚህ ስዊድን ውስጥ የማይኖሩ ከሆነ ግን እናንተን ብቻችሁን ማነጋገር እንችል እንደሆን የምንጠይቀው ሞግዚታችሁን (gode man) ነው የሚሆነው። ወላጆች ወይም ሞግዚታችሁ በሌሉበት፣ እናንተ ብቻችሁን ጉዳያችሁን ከያዘው የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤቱን ሰራተኛ ጋር መነጋገር የምትፈልጉ ከሆነ ግን ይህንኑ ማሳወቅ ያስፈልጋል።

አስተርጉዋሚ

በስዊድንኛ የሚነገሩ ቃልና ጽንሰ-ሃሳቦች በእርስዎ በራስዎ ቋንቋ ያለው ትርጓሜ የተለያየ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የራስዎን ውስጣዊ ስሜትና የደረሰብዎትን ጥቃት ሲያስረዱ ለምን በፍርሃት ውስጥ እንዳሉና ጥቃቱ በምን መንገድ ከፍርሃትዎ ጋር እንደሚዛመድም መግለጽ አስፈላጊ ነው።

አስተርጉዋሚው የሚናገረው ግልጽ ካልሆነልዎት ወይም አስተርጓሚው እርስዎ የሚነገሩትን በሙሉ ለማንም ሳይወግን የማይተረጉም ከመሰልዎት ይህንኑ፣ ጉዳይዎን ለያዘው ጸሐፊ ማሳወቅ ያስፈልጋል። አስተርጓሚው ራሱ የወሲብ ዝንባሌን የሚዳስሡ፣ ራስዎን የሚገልጹበት የጾታ ወገን ወይም የጾታ ማንነትዎን ሊያብራሩ የሚችሉትን የተለዩ ቃላት፥ ሁሌም ያውቃቸዋል ማለት እንዳልሆነ ልትገነዘቡና ልታስቡበት ይገባል። ስለዚህ አንድ ቃል ሲጠቀሙ፥ ያ ቃል በእርስዎ በኩል ትርጓሜው ምን እንደሆነ ወይም ምን ማለት ፈልገው እንደሆነ፥ ለአስተርጉዋሚው በደንብ ቢያብራሩለት ጥሩ ይሆናል ማለት ነው።

መኖሪያ ቦታ

በአብዛኛዎቹ የስደተኞች ጽ/ቤት የሚያዘጋጃቸው መኖሪያ ቦታዎች ውስጥ ሁለት ሶስት ተመሳሳይ ጾታ ያላችው ሰዎች አንድ ክፍል የሚጋሩበት ሁኔታ አለ። የጥገኝነት ጥያቀው መልስ እስኪያገኝ በሂደት ላይ ባለበት ግዜ ውስጥ፥ እርስዎ ያሉበት የአኗኑዋር ሁኔታ እየከበደ ሊመጣና፥ በመሃል በኗሪዎቹ መካከል አለመግባባትና ግጭት ሊፈጠር ይችላል ።

እንዲህ ዓይነት ችግር ሲከሰት፣ ምን እንዲደረግ እንደምትፈልጉ ወይም በምትኖሩበት ክፍል ውስጥ ደህንነት የማይሰማችሁ ከሆነ፥ በተቻለ ፍጥነት መናገር አስፈላጊ ነው። በምትኖርበት ቤት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ችግር ካጋጠሞትና ለችግሩ እንዳች መፍሄ የሚሹ ከሆነ፣ ይህኑ መናገር ይገባዎታል። ይህን በተመለከተ ከተመዘገቡበት የመኖሪያ ተቋም ውስጥ ያለው የእንግዳ መቀብያ ዘንድ ሀደው ወይም አስተዳዳሪውን አግኝተው ያነጋግሩ።

ጤና

በአንዳንድ ከተሞች ውስጥ ለተለዩ የህብረተ ሰብ ክፍሎችን ብቻ፣ ለምሳሌ የወሲብ ጤናን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ የሚያስተናግዱና ምክር የሚሰጡ የጤና ጣቢያዎች እሉ። ለምሳሌ ያህል የሚጠቀሱት የህብረተ ሰብ ክፍሎች፣ ሴቶች፣ ታዳጊ ወጣቶች ወይም ወጣ ያለ የወሲብ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች (hbtq-personer) ሲሆኑ፣ ይህን በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ጉዳይዎን የያዘውን ጸሃፊ ይጠይቁ።

በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች

የጥገኝነት ጥያቀዎ በሂደት ላይ ባለበት ግዜ ወስጥ፣ ሁሌም በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶችን እግኝተው ምክር እና ድጋፍ የመውሰድ መብት አለዎት። እርስዎ ያለዎትን መብትና የተለያዩ እማራጮች የበለጠ ባወቁ ቁጥር፣ የጥገኝነት ጥያቄዎን በተመለከተ በተለያዩ ደረጃዎች ሊገጥምዎ ለሚችል ማንኛውም ነገር የበለጠ ዝግጁ ሆነው ይገኛሉ። (RFSL) የሚባለው ማህበር አንድ በጎ ፈቃድኛ ድርጅት ሲሆን ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የወሲብ ዝንባሌ ላላቸውን ሰዎች (hbtq-personers) መብቶች ይሙዋገታል፣ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የወሲብ ዝንባሌ ላላቸው ጥግኝነት ጠያቂዎች ልዩ ድጋፍና ለመወያየት በሚፈልጉበት ግዜ የሚሰበሰቡበት ቦታ የሚያዘጋጅ ነው።

ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የወሲብ ዝንባሌ ያላቸው አዲስ መጦች ማህበር (RFSL Newcomers) External link, opens in new window.

RFSL Ungdom, Newcomers youth External link, opens in new window.

Last updated: